Posts

Showing posts from March, 2025

ብልሁ ሰዓሊ

Image
ብልሁ ሰዓሊ አንድ ዓይና የሆነ አንድ አምባገነን ሱልጣን ሦስት ሰዓሊያንን ጠርቶ የእሱን ምስል በስዕል ቀርጸው እንዲያስቀምጡለት ካሳሰባቸው በኋላ አያይዞም መጥፎ እይታ ያለው አድርጎ የሳለኝን እቀጣለሁ፡፡ በጥሩ ሁኔታ የሳለውን ደግሞ እሸልማለሁ ሲል አስጠነቀቃቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰዓሊ ሱልጣኑ አንድ ዓይና መሆኑን አጋልጦ የሚያሳይ ስዕል አድርጎ ሳለው፡፡ የሱልጣንነቱን ክብር የሚነካ በመሆኑ ቅጣት ተላለፈበት፡፡ ሁለተኛው ሰዓሊ ደግሞ ሱልጣኑ ሁለት ዓይን እንዳለው አስመስሎ ሳለው፡፡ ይኸ ሰዓሊም ሱልጣኑን የማታለል ስራ ስለሆነ የሠራው ቅጣቱን ተቀበለ፡፡ ሶስተኛው ሰዓሊ ግን የጎንዮሽ እይታ እንዲሰጥና ደናውን ዓይኑን አጉልቶ በሚያሳይ ሁኔታ ሳለው፡፡ በዚህም ሱልጣኑ ተደስቶ የወርቅና የክብር ሽልማቱን አበረከተለት፡፡  ‹‹››‹‹›› አንዳንድ ጊዜ እውነትን እውነት ማለት በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ ወይም በሌላ አባባል እውነት እራቁቷን ስትቀርብ የሚቀበላት ትንሽ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ደረቅ እውነታ ካልተዋዛ ለመዋጥ ያስቸግራል፡፡ እውነትነቱ ባይቀየርም፡፡ እውነትን ለመመስከር እውነት ሰሚ ጀሮ ያስፈልጋል፡፡ እውነትን አድማጭ በሌለበት ባዶ ሜዳ ላይ መለፍለፍ ደግሞ ከእውነት ጋር አዘቅት መግባትና ዋጋ-ቢስ መሆን ነው፡፡ በዋጋ-ቢስ እውነትና በሐሰት መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ ርቀቱ የጋት ያህል ነው ይላሉ እውቁ የንግድ ሰው ወልደሔር ይዘንጋው በግለ ታሪክ መጽሐፋቸው፡፡

ገረዲቱ - ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት

Image
ገረዲቱ እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ በጎም ሆነ ደግ ታሪክ ሳይስተናገድበት አያልፍም፤ በሥነ ፍጥረት ታሪክ ውስጥ ብትመለከቱ ምንም ሳይሠራ ያለፈ ሰው ታገኙ ይሆናል እንጅ ምንም ሥራ ያልተሠራበት ቀን አታገኙም፤ ምክንያቱም ጊዜ የተፈጠረው ለሥራ ነውና:: ከመጀመሪያዋ ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር ያላ ሥራ ያሳለፋት ጊዜ አትገኝም፡፡ በእያንዳንዳችንም ሕወት ውስጥ እለታት የየራሳቸው የሆነ ልዩ ልዩ ታሪክ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ የወደቅንባቸው አንዳንዶቹ የተነሣንባቸው፣ የተደሰትንባቸውና ያለቀስንባቸው፣ እግዚአብሔርን  ያገኘንባቸው ወይም ከሰይጣን ጋር ማኅበርተኛ የሆንባቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡  ለዛሬው እንኳን ይህን የምላችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፊ ታሪክ ስለተመዘገበለት አንድ ቅዱስ ሰው ልነግራችሁ ፈልጌ ነው፤ ሰውየው ገሊላዊ፣ ትውልዱና ነገዱ ዕብራዊ ሲሆን ያደገው በታላቁ የገሊላ ባሕር አጠገብ ነው ዋና ሥራው አሣ አጥማጅነት ሲሆን የቀደመ ስሙ ስምዖን ወልደ ዮና የክርስትና ስሙ ደግሞ ጴጥሮስ ይባላል፡፡ ይህ ሰው እግዚአብሔር በእርጅና ዘመኑ የባረከው ሰው ነው፤ መቸም እግዚአብሔር ለእያንዳንደችን ያዘጋጃት የመጎብኘት ቀን እንዳለች እናምናለን፣ ከዚህም የተነሣ አንዳንዶችን  በማሕጸን ሳሉ እንደነ ኤርምያስና ዮሐንስ መጥምቅ ያሉትን፣አንዳንዶችን በጨቅላነት እድሜ እንደነ ቅዱስ ቂርቆስ፣ አንዳንዶችን በወጣትነት እንደነ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊና እንደነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያሉትን አንዳንዶችን በእርጅና ዘመናቸው እንደነ ቅዱስ ጴጥሮስ ያሉትን ጎብኝቷቸዋል ፡፡ ከሰው የሚጠበቅ የሚጎበኝበትን ቀን ደጅ መጥናት ነው እንጅ ሌላው የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እግዚአብሔር የወሰነለት ቀን ስትደርስ በትጋት ሆኖ ከሚሠራበት ቦታ ሂዶ ጎበኘው፣ ለ...