ከክፍል 2 የቀጠለ.... Part 1 link , part 2 link ‹‹ስለአንተ ሁሉን ነገር ነግሬዋለሁ፡፡ ከተዋወቅን ስድስት ወር እንደሆነን… ስንቀሳቀስ ሁሌም የአንተን ባጃጅ እንደምጠቀም… የምፈልገው ቦታ እንደምታደርሰኝና እንደምትመልሰኝ… ከለካፊዎች እንደምትጠብቀኝ… እንደምታዝናናኝ… እንደምታጫዉተኝ… ባጃጅ መንዳት እንደምታለማምደኝ… እና ደግሞ…›› የጀመረችውን ዓረፍተ ነገር ሳትጨርሰው አይኗን እንደጨፈነች ተመስጣ ጥርሷን ብቻ ስታሳየኝ ቆየች፡፡ ከዚያ አይኞቿ ተከፈቱ፡፡ ‹‹…እና ደግሞ… እንደ.ም.ወ.ድ.ህ ጭምር!›› በጠራራ ፀሀይ… ወለል ባለ ብርሀን… የሚርመሰመስ ህዝብና መኪና ባለበት መንገድ ዳር… በዚህ ሁሉ መሀል እኔነቴን ማን ዘረፈኝ? ድምፄንስ ምን ዘጋው? ምክንያቱን ሳላውቀው ድጋሚ ጸጥ አልኩ፡፡ ድርቅ እንደ እንጨት! ከኋላየ መጥታ እጇን ጫን ስታደርግብኝ ባለሁበት ቅዠቴ ጀመረኝ፡፡ የተቀደሰ ቅዠት፡፡ ቅዠቱ እንዲህ ሲል ይጀምራል፡- እኔና ሳሮን ነጭ በነጭ ሙሉ የባህል ልብስ ለብሰን፣ መላዕክቱን መስለን በተቆናጀች ባጃጄ ወደ አባቷ ቤት እንቀርባለን፡፡ አባቷ ነጭ በነጭ የሆነ ሙሉ የባህል ልብስ ለብሰው የቤታቸው ሰገነት ላይ በሩቁ ይታዩናል፡፡ የሆኑ ከየት መጡ ያላልናቸው ሁለት ነጭ መለዮ የለበሱ ሰዎች ሳሮንና እኔን ግራና ቀኝ አጅበው ወደ አባቷ አቀረቡን፡፡ /ያ-ቅዠት የት ሄደ? ያ- የሰይጣኖቹ?/ ሳሮን እሮጣ ሄዳ አባቷን ጥምጥም ብላ ከሳመቻቸው በኋላ ወደኔ እየጠቆመች ‹‹አባየ የነገርኩህ ልጅ ይኼ ነው›› ስትላቸው ከሳሮን በፈጠነ ሮጬ እግራቸው ስር ተደፍቼ ጉልበት ሳምኩ፡፡ ከየት መጣ ያላልኩት ወታደር ከእግራቸው ስር ለአክብሮት የተንበረከክሁትን እኔን በአንድ እጁ አንጠልጥሎ አነሳኝ፡፡ እንደ ሁኔታው እንዳንጠለጠለኝ ሊወረውረኝ ያሰበ ይመስል ነ...
Comments
Post a Comment