ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው

 ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት  በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው። ስሙም ፒተር ይባላል፡፡ አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ። ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና 'ርግብ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" ሲላቸው ብልሁ ማንዴላም "አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብለዋቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ። በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል። አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ፡-

"ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ ገንዘብ' በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ 'ጥበብ' ቢኖር የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ሲጠይቀው

ማንዴላም "ገንዘቡን እወስደዋለሁ" ብሎ መለሰለት። ፕሮፌሰሩም በድል አድራጊነት "አንተ ሞኝ ነህ፣ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ እወስድ ነበር" ሲለው ማንዴላ ፈገግ እያለ "ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው። በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ፡፡ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ "ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ረስተኸዋል" ብሎት እርፍ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ገረዲቱ - ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት

የህልሜ ጓደኛ 3

የህልሜ ጓደኛ 2