Posts

Showing posts with the label best story

ፈጣሪ ሆይ አትማረኝ!

Image
በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ጫካ ውስጥ ብቻዋን የምትኖር ወጣት ነበረች። ሁልጊዜ ጥዋት ጥዋት እየተነሳች ወደ ባህር ዳርቻ በመሄድ ‹‹ፈጣሪ ሆይ አትማረኝ! አትማረኝ!›› እያለች ትፀልያለች። ታድያ ከባህሩ መሀል ላይ ካለች ደሴት ላይ የሚኖር አንድ ወጣት ይህችን ልጅ ፀሎት ሁልጊዜ ይሰማና ይገረም ነበር። ‹‹ወይ አለማወቅ›› ብሎም ከራሱም ጋር ያወራ ነበር። እና አንድ ቀን ይህች ሴት እንደተለመደው ወደ ባህሩ ዳርቻ ሄዳ ስትፀልይ ያያት ያ ወጣት በትንሽ ታንኳ(ጀልባ) ተሳፍሮ ወደ ባህሩ ዳርቻ ይሄድና ‹‹አንቺ ሴት ሁልጊዜ አትማረኝ አትማረኝ እያልሽ ስትፀልይ እሰማለሁ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም አላዋቂነት ነው። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ‹ማረኝ ማረኝ ማረኝ› እያልሽ ነው መፀለይ ያለብሽ›› ብሏት በመጣበት አቅጣጫ ተመለሰ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይህች ሴት ‹‹ቆይ ይህ ወጣት ምን ብለሽ ነበር ፀልይ ያለኝ… እረሳሁት›› ብላ በባህሩ ላይ እየሮጠች ጀልባዋ ጋር ከደረሰች በኋላ ‹‹ወንድም ሆይ የነገርከኝን ረሳሁት፤ ምን ብለሽ ነበር ፀልይ ያልከኝ?›› ስትል ጠየቀችው? ይህ ወጣትም በባህሩ ላይ መሮጥ መቻሏን አይቶ በጣም በመደነቅ እና በመደመም ‹‹በይ እህቴ ቀድሞ ስትፀልይ እንደነበረው ፀልይ›› አላት ይባላል። ምን ለማለት ፈልጌ ነው አንተ ትክክል ነው ብለህ ያመንክበትን ነገር ያለምንም ማፈር ወይም መሸማቀቅ አድርገው ወይም ተግብረው። ሌሎች ሰዎች በእነሱ አተያይና አመለካከት ሊቃኙህ ቢሞክሩ ፍፁም እንዳትሰማቸው። ትክክል ነኝ ብለህ ካመንክበት በቃ አድርገው።

ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው

Image
 ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት  በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው። ስሙም ፒተር ይባላል፡፡ አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ። ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና 'ርግብ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" ሲላቸው ብልሁ ማንዴላም "አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብለዋቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ። በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል። አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ፡- "ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ ገንዘብ' በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ 'ጥበብ' ቢኖር የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ሲጠይቀው ማንዴላም "ገንዘቡን እወስደዋለሁ" ብሎ መለሰለት። ፕሮፌሰሩም በድል አድራጊነት "አንተ ሞኝ ነህ፣ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ እወስድ ነበር" ሲለው ማንዴላ ፈገግ እያለ "ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው። በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ፡፡ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ "ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ረስተኸዋል" ብሎት እርፍ፡፡

ገረዲቱ - ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት

Image
ገረዲቱ እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ በጎም ሆነ ደግ ታሪክ ሳይስተናገድበት አያልፍም፤ በሥነ ፍጥረት ታሪክ ውስጥ ብትመለከቱ ምንም ሳይሠራ ያለፈ ሰው ታገኙ ይሆናል እንጅ ምንም ሥራ ያልተሠራበት ቀን አታገኙም፤ ምክንያቱም ጊዜ የተፈጠረው ለሥራ ነውና:: ከመጀመሪያዋ ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር ያላ ሥራ ያሳለፋት ጊዜ አትገኝም፡፡ በእያንዳንዳችንም ሕወት ውስጥ እለታት የየራሳቸው የሆነ ልዩ ልዩ ታሪክ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ የወደቅንባቸው አንዳንዶቹ የተነሣንባቸው፣ የተደሰትንባቸውና ያለቀስንባቸው፣ እግዚአብሔርን  ያገኘንባቸው ወይም ከሰይጣን ጋር ማኅበርተኛ የሆንባቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡  ለዛሬው እንኳን ይህን የምላችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፊ ታሪክ ስለተመዘገበለት አንድ ቅዱስ ሰው ልነግራችሁ ፈልጌ ነው፤ ሰውየው ገሊላዊ፣ ትውልዱና ነገዱ ዕብራዊ ሲሆን ያደገው በታላቁ የገሊላ ባሕር አጠገብ ነው ዋና ሥራው አሣ አጥማጅነት ሲሆን የቀደመ ስሙ ስምዖን ወልደ ዮና የክርስትና ስሙ ደግሞ ጴጥሮስ ይባላል፡፡ ይህ ሰው እግዚአብሔር በእርጅና ዘመኑ የባረከው ሰው ነው፤ መቸም እግዚአብሔር ለእያንዳንደችን ያዘጋጃት የመጎብኘት ቀን እንዳለች እናምናለን፣ ከዚህም የተነሣ አንዳንዶችን  በማሕጸን ሳሉ እንደነ ኤርምያስና ዮሐንስ መጥምቅ ያሉትን፣አንዳንዶችን በጨቅላነት እድሜ እንደነ ቅዱስ ቂርቆስ፣ አንዳንዶችን በወጣትነት እንደነ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊና እንደነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያሉትን አንዳንዶችን በእርጅና ዘመናቸው እንደነ ቅዱስ ጴጥሮስ ያሉትን ጎብኝቷቸዋል ፡፡ ከሰው የሚጠበቅ የሚጎበኝበትን ቀን ደጅ መጥናት ነው እንጅ ሌላው የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እግዚአብሔር የወሰነለት ቀን ስትደርስ በትጋት ሆኖ ከሚሠራበት ቦታ ሂዶ ጎበኘው፣ ለ...