ፈጣሪ ሆይ አትማረኝ!
በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ጫካ ውስጥ ብቻዋን የምትኖር ወጣት ነበረች። ሁልጊዜ ጥዋት ጥዋት እየተነሳች ወደ ባህር ዳርቻ በመሄድ ‹‹ፈጣሪ ሆይ አትማረኝ! አትማረኝ!›› እያለች ትፀልያለች።
ታድያ ከባህሩ መሀል ላይ ካለች ደሴት ላይ የሚኖር አንድ ወጣት ይህችን ልጅ ፀሎት ሁልጊዜ ይሰማና ይገረም ነበር። ‹‹ወይ አለማወቅ›› ብሎም ከራሱም ጋር ያወራ ነበር።
እና አንድ ቀን ይህች ሴት እንደተለመደው ወደ ባህሩ ዳርቻ ሄዳ ስትፀልይ ያያት ያ ወጣት በትንሽ ታንኳ(ጀልባ) ተሳፍሮ ወደ ባህሩ ዳርቻ ይሄድና ‹‹አንቺ ሴት ሁልጊዜ አትማረኝ አትማረኝ እያልሽ ስትፀልይ እሰማለሁ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም አላዋቂነት ነው። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ‹ማረኝ ማረኝ ማረኝ› እያልሽ ነው መፀለይ ያለብሽ›› ብሏት በመጣበት አቅጣጫ ተመለሰ።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይህች ሴት ‹‹ቆይ ይህ ወጣት ምን ብለሽ ነበር ፀልይ ያለኝ… እረሳሁት›› ብላ በባህሩ ላይ እየሮጠች ጀልባዋ ጋር ከደረሰች በኋላ ‹‹ወንድም ሆይ የነገርከኝን ረሳሁት፤ ምን ብለሽ ነበር ፀልይ ያልከኝ?›› ስትል ጠየቀችው?
ይህ ወጣትም በባህሩ ላይ መሮጥ መቻሏን አይቶ በጣም በመደነቅ እና በመደመም ‹‹በይ እህቴ ቀድሞ ስትፀልይ እንደነበረው ፀልይ›› አላት ይባላል።
ምን ለማለት ፈልጌ ነው
አንተ ትክክል ነው ብለህ ያመንክበትን ነገር ያለምንም ማፈር ወይም መሸማቀቅ አድርገው ወይም ተግብረው። ሌሎች ሰዎች በእነሱ አተያይና አመለካከት ሊቃኙህ ቢሞክሩ ፍፁም እንዳትሰማቸው። ትክክል ነኝ ብለህ ካመንክበት በቃ አድርገው።
Comments
Post a Comment