Posts

የከሸፈ ትውልድ 1

Image
ክፍል 1 - Part 1 ጥሎብኝ በተለያዩ ምክንያቶች ራቅ ወዳሉ ቦታዎች በህዝብ ትራንስፖርት ስንቀሳቀስ ሴቶች ጋር ብቀመጥ እመርጣለሁ፡፡ በተቻለኝ አቅምም ሴቶች ጋር ለመቀመጥ አመቻቻለሁ፡፡ ‹‹የሆነ የሴት ዛር ሳይለክፍህ አይቀርምኮ…›› ይሉኛል ጓደኞቼ፡፡ እኔ ግን አሁንም እደግመዋለሁ! ምርጫዎቼ ሴቶች ናቸው፡፡ ወዳጄ ያለ ሴቶች መንገዱ ብቻ ሳይሆን ህይወትም ባዶ ትመስለኛለች፡፡ ከስንት አመት በፊት ያኔ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እያለን በጾታ እኩልነት/ጀንደር/ ዙሪያ ስንወያይ ከመካከላችን ፍልስፍናውን እዉቅና የሰጠንለት አንድ ተማሪ እንዲህ ሲል ተከራከረ፡፡ ‹‹female is unfinished creature. ሴቶች ዉጥን ፍጡሮች ናቸው! ገባህ አንድ አካል ሙሉ እንዲሆን ከሚሰራበት ቁስ /elemenet/ ከእያንዳንዱ የሚያስፈልገዉን ያህል መጠን ወስደህ መገጣጠም ይኖርብሃል፡፡ ለምሳሌ ዉሃን እንመልከት! ዉሃ ዉሃ እንዲሆን /በፕላስቲክ ጠርሙስ የያዘዉን የታሸገ ዉሃ ከፍ አድርጎ እያሳየን/ ሁለት እጅ ሃይድሮጅንና አንድ እጅ ኦክስጅን ነው የምንጠቀመው፡፡ መጠኑ ከዚህ ከፍ ወይም ዝቅ ቢል ግን በፍጹም ዉሃን አትሰራዉም፡፡ አየህ!… ሴት ግን ከዚህ በታች ናት፡፡ ለምን? የሚል ጥያቄ ልትጠይቅ ትችላለህ፡፡ ምክንያቱም አዳም ከተሰራበት ነገር አንድ በአንድ መካፈል ነበረባት፡፡ ከደሙ ደም፣ ከስጋው ስጋ፣ ከአጥንቱ አጥንት ስትወስድ ነው ሙሉ ሰው የምትባለው፡፡ እሷ ግን ከቁራጭ አጥንት ብቻ ነው የተሰራችው!›› ሲል ተከራከረ፡፡ መከራከር ብቻም ሳይሆን ምንጩ እዉነት መሆኑን እስካሁን ባናረጋግጥም እሱ ግን እዉቁ ፈላስፋ ኒቼ እንደተናገረው በልበ ሙሉነት ነገረን፡፡ እንዲህ ሲፈላሰፍብን ሁላችንም ከልባችን ነበር የምናዳምጠው፡፡ በዚያች ቅጽበት ለብቻው መድረኩን ተቆጣጥሮት የነበረው ...