ከላሊበላ ሰማይ ስር Lalibela
አሁን ይህንን ስጽፍልህ 100 ግራም ገለምሶ ይዤ ከተቀመጥኩበት ቦታ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ አንተም ከዚህ የተለየ ነገር እያደረግህ እንዳልሆነ ስነግርህ ያለጥርጥር ነው፡፡ ግድ የለም በርጫ ሙድ ላይ አይደለህም እንበል…ግን የሰፈር አረቄ ቤት ዉስጥ አረቄን በሲጋራና በአሉባልታ እያወራረድክ ነው፡፡ እሱ ላይ ባትሆንም ደግሞ መንገድ ላይ ድድ እያሰጣህ አላፊ አግዳሚ ታሸማቅቃለህ…ትለክፋለህ፣ትስቃለህ……መሳቂያ!!!
በሌለንበት
በሃሜት… ላልከኝ ወዳጄ ደግሜ እልሃለሁ አትፍራ ከማማት ልቆጠብና
ቢሮ ዉስጥ ነህ እንበል ግን ቢሮህ ዉስጥ ብትሆንም ወንበር እያለፋህ የምሳ ሰዓት መድረስን ትጠባበቅ ይሆናል ወይም ደግሞ ልክ እንደ
ጀበና ቡና ኮምፒተር ላይ ተጥደሃል ማለቴ ፌስ ቡክ ላይ፡፡
እና
እልሃለሁ ቢሮ ዉስጥ ሆነህ ስራ ካልሰራህ ጫት ቤት ከተቀመጠው … መንገድ ላይ ድድ ከሚያሰጣው በምን ልለይህ…አረቆ ከሚጋተውስ በምን
ተሸልክ….በምንም!! ብቻ የትም ሁን የት ብትሰራም ባትሰራም ቅሉ የዚህ ትዉልድ አባል ነህ፡፡
ይቅርታ
የስድብ ናዳ አወረድኩኝ ልበል ምን ላድርግ በቆምኩበት ብትቆሙ ያየሁትን ብታዩኮ እንደ እሳት ላንቃ የሚገርፍ የማንነት ስሜት ከዉስጣችሁ
ሲገነፍል ታዩት ነበር፡፡
ወዳጄ
አሁን በላሊበላ ተራሮች ስር ነኝ፡፡የንጉስ ላሊበላ የእጅ ስራና ጥበብ ካረፈባቸው ድንቅ ዉቅሮች ስር፡፡ ግን ምን ያደርጋል ማመን
አቃተኝ፡፡
-የሰው
ልጅ እንዴት ከአንድ ድንጋ እነዚን ግዙፍ አቢያተክርስቲያናት ሊሰራ ይችላል….እኛምኮ የሰው ዘሮች ነን አዷማ ይዘን፣በዲጅኖ ታግዘን
በመዶሻ ደብድነብ ሜ አንድ ሜትር ድንጋይ ፈለጥንና
-እነዚ
በድንጋይ ላይ የተጠረቡ ቅርጻቅርጾችና አምሳላት እንዴት እዉን ሊሆኑ ቻሉ
-እነዚያ
900 በላይ አመታትን ያስቆጠሩ ስዕላት እንዴት ቀለማቸው እንደደመቀ ኖረ….በምን ሚስጥር
-ዛሬ
አሸዋን በስሚንቶ አዋህደን የሰራነው ፎቅ መቼ ጠና…. ታዲያ እንዴት
ወጥ ከሆነ የድንጋይ ተራራ የዳሩ ሳናድ የመሃሉ እንደጠና ቅርጽ ይዞ ቆመ
-ቅዱስ
ላሊበላ እነዚን 11 ቤተ መቅደሶች የፈለፈለ በምን ተዓምር ይሆን
-የድንጋይ
ወጋግራ፣የድንጋይ ማገር፣የድንጋይ ምሰሶ…እንዴት ሆኖ…………
ከቦታዉ
ቆሜ እነዚያን የድንጋ ደብሮች ባየሁ ጊዜ አይኔ ማመን አቃተው…ሰው በአይኑ እያየ ማመን ያቅተዋል…አሁን እዚህ ቦታ ምን ስል መጣሁ…ዝም
ብየ በሩቁ የቅዱሱን የእጅ ስራዎች ባደንቅ ይሻለኝ ነበር አልኩኝ
ለራሴ፡፡
ይሄ
የሰው ስራ ኤደለም
የተፈጥሮም
አይመስለኝም
መላዕክትም
አልገነቡትም…..እንዲህ ብቻየን ስፈላሰፍ….
ታዲያስ
ምን ይመስልሃል አሉኝ አስጎብኝየ አባ ሃይለ ጊዮረጊስ ቀኑን ሙሉ የነገሩኝን እውነት ገደል ስከትባቸው ጊዜ ገርሟቸው፡፡
እኔ
እንጃ…..አላዉቅም እንዴት እንደተሰሩ……/እንደዚህ ቀን ገራ ገብቶኝ አያዉቅም/
ምን
ታደርግ አልፈርድብህም አንተምኮ የዚህ ጠማማ ትዉልድ አካል ነህ አሉኝ
በቃ
መልሱ ተመለሰ……ጠማማ ትዉልዶች……ወይ አንሰራ …ወይ የሰሩትን አናምን… አይ እኛ!!!

Comments
Post a Comment