ሳያስቡ ከመኖር እያሰቡ መሞት ይሻላል
እጅግ አስቀያሚ መልክ ያለው፣ ትልቅ መላጣ ራስ፣ ትንሽ ፊት፣ ረጅም ቅጥ ያጣ ፂም፣ ጨቅጫቃ ሚስት የነበረው እና ሲበዛ ተከራካሪ እና
ተጫዋች ነው።
ገና በጠዋቱ ማልዶ ተነስቶ ቁርሱን በልቶ፣ አሮጌ ልብስ ለብሶ በባዶ እግሩ ወደ ከተማ ሄዶ ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አስገራሚውን አዲስ ሃሳብ አካፈፍሎ ማታ ላይ ከገበያተኛው ጋር ባዶ እጁን ወደ ቤቱ ይመለስ ነበር። ግሪክ የእውቀት አማልዕክት መናፍስት የመረቋት፣ ሃሳብ የተፀነሰባት እና የተወለደባት ብቻ ሳትሆን ሃሳብ የተከበረባት ውብ ሃገር ነች። ከዛሬ 2500 ዓመት በፊት ስልጡን ህዝብ የሚኖርባት ለአዲስ አስተሳሰብ ትልቅ ዋጋ (credit) ሰጥታ ሃሳብ የሚወለድባቸው አደባባዮች የገነባች የጠቢባን ምድር ግሪክን አለማድነቅ ምቀኝነት ነው። ህዝቡስ ቢሆን ፍቅር ነው.... አዲስ ሃሳብ ለመስማት ስራየ ብሎ አደባባዮችን ያጨናንቅ ነበር። ማንም አዲስ ሃሳብ ያለው ሰው ወጥቶ ሃሳቡን በነጻነት ይናገር ነበር። የእኛ ህዝብ አዲስ ሃሳብ መስማትም ማመንጨትም አይወድም.... ትልቁ የሃገሪቱ ራስ ምታት ይኸው ነው። አሪዮስ ፋጎስ በሚባለው መድረካቸው የጠቢባን ጥበብ እንደጉድ ይፈሳል። ቅዱስ ጳውሎስም አዲስ ሃሳብ አለኝ ብሎ በመውጣት በሚገባ ኢየሱስን ሰብኮላቸዋል። ከሶቅራጥስ በፊት ከቴለስ እስከ ሄራክሊተስ ድረስ ስለ ዓለማት ዓፈጣጠር cosmology ይጠይቁ ይመራመሩ ነበር። ሶቅራጥስ መጣና ስለ ህዋ(space) ማጥናት ብዙም አያዋጣም ሁሉም እውቀት፣ እውነት እና ጥበብ ያለችው ከሰው ውስጥ ነው አለ። ይተነትነው ገባ.... የግሪክን ወጣቶች ቀልብ ያለ ምንም ጠቅልሎ ማረከ፣ ቆነጃጅት በሶቅራጥስ ጥበብ መነኮሱ፣ አማልክቶች ሁሉ ለሶቅራጥስ ሃሳብ እጅ ሰጡ.... ዓለምን ከብርቱ ድባቴ ቀሰቀሳት፣ አዛወንቶች ቆዘሙ፣ ሶቅራጥስ
ይሙት አሉ። ከእስር የማምለጥ ሙሉ አቅም እያለው ‹‹እኔ ኖሬ ውሸት ከሚነግስ እኔ ሞቸ እውነት ትኑር›› ብሎ የሄሞሎክ መርዝን ጠጣው እና እያሰበ ወደ ዘላለም ዝምታ ነጎደ..... ሃሳብ ካልፈተንን፣ ሃሳብ ካልወለድን፣ ሃሳብ ካላከበርን፤ እውቀት፣ ጥበብ እና እውነት ካልተከበሩ የሰው ትርጉሙ ያንሳል። ሃገርም እርሟን ታውጣ ......
Comments
Post a Comment