ሳስበው ደከመኝ
ሴትን ልጅ ስትመርጣት አጋር ለህይወትህ
ዉስጥ ዉበቷን እንጂ ዉጯ እንዳያስትህ
እኔም እንዲሁ ነኝ
ዉበት ረጋፊ ነው
ዉስጤን ተመልከተኝ
ብለሽኝ ነበረ…
ግና…..
ከባለጌ ጡትሽ መረን ከለቀቀው
ከቀዩ ከንፈርሽ ከተለቀለቀው
ከሸምበቆ ባትሽ እንደ ፍም ከቀላው
ከፌዘኛ ሳቅሽ አዉሬ ከሚያስበላው
ከአሽሙረኛ ዳሌሽ በኩራት ከሰፋው
ከሱናሜ ጥቅሻሽ መንገድ ከሚያስጠፋው
፤፤
፤፤
ዙሪያ ገባሽ ሁሉ ከልሎት የአጋም ሾህ
አጥረሽው በአጣና
በየት አልፌ ነው ጸባይሽን የማየው
ውስጥሽን ማጠና!?
እ…..
ሳስበው ደከመኝ!!!
ዉስጥ ዉበቷን እንጂ ዉጯ እንዳያስትህ
እኔም እንዲሁ ነኝ
ዉበት ረጋፊ ነው
ዉስጤን ተመልከተኝ
ብለሽኝ ነበረ…
ግና…..
ከባለጌ ጡትሽ መረን ከለቀቀው
ከቀዩ ከንፈርሽ ከተለቀለቀው
ከሸምበቆ ባትሽ እንደ ፍም ከቀላው
ከፌዘኛ ሳቅሽ አዉሬ ከሚያስበላው
ከአሽሙረኛ ዳሌሽ በኩራት ከሰፋው
ከሱናሜ ጥቅሻሽ መንገድ ከሚያስጠፋው
፤፤
፤፤
ዙሪያ ገባሽ ሁሉ ከልሎት የአጋም ሾህ
አጥረሽው በአጣና
በየት አልፌ ነው ጸባይሽን የማየው
ውስጥሽን ማጠና!?
እ…..
ሳስበው ደከመኝ!!!
Hab. A
Comments
Post a Comment