Posts

Showing posts from December, 2025

ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ

Image
✍ ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው። በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንህ በሰው ከደረሰበት ትማራለህ፣ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ። ✍ የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል። ✍ ዓይንህ የፊቱን ቢያይ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ፡፡  ምክረ አበው

ፈጣሪ ሆይ አትማረኝ!

Image
በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ጫካ ውስጥ ብቻዋን የምትኖር ወጣት ነበረች። ሁልጊዜ ጥዋት ጥዋት እየተነሳች ወደ ባህር ዳርቻ በመሄድ ‹‹ፈጣሪ ሆይ አትማረኝ! አትማረኝ!›› እያለች ትፀልያለች። ታድያ ከባህሩ መሀል ላይ ካለች ደሴት ላይ የሚኖር አንድ ወጣት ይህችን ልጅ ፀሎት ሁልጊዜ ይሰማና ይገረም ነበር። ‹‹ወይ አለማወቅ›› ብሎም ከራሱም ጋር ያወራ ነበር። እና አንድ ቀን ይህች ሴት እንደተለመደው ወደ ባህሩ ዳርቻ ሄዳ ስትፀልይ ያያት ያ ወጣት በትንሽ ታንኳ(ጀልባ) ተሳፍሮ ወደ ባህሩ ዳርቻ ይሄድና ‹‹አንቺ ሴት ሁልጊዜ አትማረኝ አትማረኝ እያልሽ ስትፀልይ እሰማለሁ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም አላዋቂነት ነው። ስለዚህ ከዛሬ ጀምሮ ‹ማረኝ ማረኝ ማረኝ› እያልሽ ነው መፀለይ ያለብሽ›› ብሏት በመጣበት አቅጣጫ ተመለሰ። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይህች ሴት ‹‹ቆይ ይህ ወጣት ምን ብለሽ ነበር ፀልይ ያለኝ… እረሳሁት›› ብላ በባህሩ ላይ እየሮጠች ጀልባዋ ጋር ከደረሰች በኋላ ‹‹ወንድም ሆይ የነገርከኝን ረሳሁት፤ ምን ብለሽ ነበር ፀልይ ያልከኝ?›› ስትል ጠየቀችው? ይህ ወጣትም በባህሩ ላይ መሮጥ መቻሏን አይቶ በጣም በመደነቅ እና በመደመም ‹‹በይ እህቴ ቀድሞ ስትፀልይ እንደነበረው ፀልይ›› አላት ይባላል። ምን ለማለት ፈልጌ ነው አንተ ትክክል ነው ብለህ ያመንክበትን ነገር ያለምንም ማፈር ወይም መሸማቀቅ አድርገው ወይም ተግብረው። ሌሎች ሰዎች በእነሱ አተያይና አመለካከት ሊቃኙህ ቢሞክሩ ፍፁም እንዳትሰማቸው። ትክክል ነኝ ብለህ ካመንክበት በቃ አድርገው።

ሳያስቡ ከመኖር እያሰቡ መሞት ይሻላል

Image
እጅግ አስቀያሚ መልክ ያለው፣ ትልቅ መላጣ ራስ፣ ትንሽ ፊት፣ ረጅም ቅጥ ያጣ ፂም፣ ጨቅጫቃ ሚስት የነበረው እና ሲበዛ ተከራካሪ እና ተጫዋች ነው።  ገና በጠዋቱ ማልዶ ተነስቶ ቁርሱን በልቶ፣ አሮጌ ልብስ ለብሶ በባዶ እግሩ ወደ ከተማ ሄዶ ህዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ አስገራሚውን አዲስ ሃሳብ አካፈፍሎ ማታ ላይ ከገበያተኛው ጋር ባዶ እጁን ወደ ቤቱ ይመለስ ነበር። ግሪክ የእውቀት አማልዕክት መናፍስት  የመረቋት፣ ሃሳብ የተፀነሰባት እና የተወለደባት ብቻ ሳትሆን ሃሳብ የተከበረባት ውብ ሃገር ነች። ከዛሬ 2500 ዓመት በፊት ስልጡን ህዝብ የሚኖርባት ለአዲስ አስተሳሰብ ትልቅ ዋጋ (credit) ሰጥታ ሃሳብ የሚወለድባቸው አደባባዮች የገነባች የጠቢባን ምድር ግሪክን አለማድነቅ ምቀኝነት ነው። ህዝቡስ ቢሆን ፍቅር ነው.... አዲስ ሃሳብ ለመስማት ስራየ ብሎ አደባባዮችን ያጨናንቅ ነበር። ማንም አዲስ ሃሳብ ያለው ሰው ወጥቶ ሃሳቡን በነጻነት ይናገር ነበር። የእኛ ህዝብ አዲስ ሃሳብ መስማትም ማመንጨትም አይወድም.... ትልቁ የሃገሪቱ ራስ ምታት ይኸው ነው። አሪዮስ ፋጎስ በሚባለው መድረካቸው የጠቢባን ጥበብ እንደጉድ ይፈሳል። ቅዱስ ጳውሎስም አዲስ ሃሳብ አለኝ ብሎ በመውጣት በሚገባ ኢየሱስን ሰብኮላቸዋል። ከሶቅራጥስ በፊት ከቴለስ እስከ ሄራክሊተስ ድረስ ስለ ዓለማት ዓፈጣጠር cosmology ይጠይቁ ይመራመሩ ነበር። ሶቅራጥስ መጣና ስለ ህዋ(space) ማጥናት ብዙም አያዋጣም ሁሉም እውቀት፣ እውነት እና ጥበብ ያለችው ከሰው ውስጥ ነው አለ። ይተነትነው ገባ.... የግሪክን ወጣቶች ቀልብ ያለ ምንም ጠቅልሎ ማረከ፣ ቆነጃጅት በሶቅራጥስ ጥበብ መነኮሱ፣ አማልክቶች ሁሉ ለሶቅራጥስ ሃሳብ እጅ ሰጡ.... ዓለምን ከብርቱ ድባቴ ቀሰቀሳት፣ አዛወንቶች...

ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው

Image
 ኔልሰን ማንዴላ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የህግ ትምህርት  በሚማሩበት ጊዜ ነጭ ፕሮፌሰር አስተማሪ ነበራቸው። ስሙም ፒተር ይባላል፡፡ አንድ ቀን ፕሮፌሰር ፒተር በአንድ ምግብ ቤት ምግባቸውን እየበሉ ሳለ ማንዴላ በአጋጣሚ ምግብ ይዘው ከአጠገባቸው ይቀመጣሉ። ፒተርም "አቶ ማንዴላ! አሳማና 'ርግብ ለመብል አብረው አይቀመጡም!" ሲላቸው ብልሁ ማንዴላም "አይጨነቁ ፕሮፌሰር በርሬ እሄዳለሁ" ብለዋቸው ሌላ ወንበር ላይ ይቀመጣሉ። በዚህ የተናደደው ፒተር በሌላ ቀን ቂሙን ሊወጣበት ያስባል። አንድ ቀንም ፕሮፌሰሩ ክላስ ውስጥ እያስተማሩ፡- "ማንዴላ በመንገድ ላይ እየሄድክ ሁለት ቦርሳዎችን ብታገኝና በአንደኛው ቦርሳ ገንዘብ' በሌላኛው ቦርሳ ደግሞ 'ጥበብ' ቢኖር የትኛውን ትወስዳለህ?" ብሎ ማንዴላን ሲጠይቀው ማንዴላም "ገንዘቡን እወስደዋለሁ" ብሎ መለሰለት። ፕሮፌሰሩም በድል አድራጊነት "አንተ ሞኝ ነህ፣ እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ጥበብ ያለበትን ቦርሳ እወስድ ነበር" ሲለው ማንዴላ ፈገግ እያለ "ልክ ነህ ማንም የሌለውን ነው የሚወስደው" አለው። በዚህ ሁሉ ነገር የተበሳጨው ፕሮፌሰር ፒተር የማንዴላ የፈተና ወረቀት ላይ 'ደደብ' ብሎ ይፅፋል። ሌሎች ተማሪዎች የታረመላቸውን የፈተና ወረቀት ሲያዩ ማንዴላ ደደብ የሚለውን ፅሁፍ ከወረቀቱ ላይ አየና ተገረመ፡፡ ከዛም ወደ ፕሮፌሰሩ ሄዶ "ይቅርታ ቲቸር ፊርማህን ብቻ ነው ያስቀመጥክልኝ ውጤቴን ረስተኸዋል" ብሎት እርፍ፡፡