Posts

ብልሁ ሰዓሊ

Image
ብልሁ ሰዓሊ አንድ ዓይና የሆነ አንድ አምባገነን ሱልጣን ሦስት ሰዓሊያንን ጠርቶ የእሱን ምስል በስዕል ቀርጸው እንዲያስቀምጡለት ካሳሰባቸው በኋላ አያይዞም መጥፎ እይታ ያለው አድርጎ የሳለኝን እቀጣለሁ፡፡ በጥሩ ሁኔታ የሳለውን ደግሞ እሸልማለሁ ሲል አስጠነቀቃቸው፡፡ የመጀመሪያው ሰዓሊ ሱልጣኑ አንድ ዓይና መሆኑን አጋልጦ የሚያሳይ ስዕል አድርጎ ሳለው፡፡ የሱልጣንነቱን ክብር የሚነካ በመሆኑ ቅጣት ተላለፈበት፡፡ ሁለተኛው ሰዓሊ ደግሞ ሱልጣኑ ሁለት ዓይን እንዳለው አስመስሎ ሳለው፡፡ ይኸ ሰዓሊም ሱልጣኑን የማታለል ስራ ስለሆነ የሠራው ቅጣቱን ተቀበለ፡፡ ሶስተኛው ሰዓሊ ግን የጎንዮሽ እይታ እንዲሰጥና ደናውን ዓይኑን አጉልቶ በሚያሳይ ሁኔታ ሳለው፡፡ በዚህም ሱልጣኑ ተደስቶ የወርቅና የክብር ሽልማቱን አበረከተለት፡፡  ‹‹››‹‹›› አንዳንድ ጊዜ እውነትን እውነት ማለት በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ ወይም በሌላ አባባል እውነት እራቁቷን ስትቀርብ የሚቀበላት ትንሽ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ደረቅ እውነታ ካልተዋዛ ለመዋጥ ያስቸግራል፡፡ እውነትነቱ ባይቀየርም፡፡ እውነትን ለመመስከር እውነት ሰሚ ጀሮ ያስፈልጋል፡፡ እውነትን አድማጭ በሌለበት ባዶ ሜዳ ላይ መለፍለፍ ደግሞ ከእውነት ጋር አዘቅት መግባትና ዋጋ-ቢስ መሆን ነው፡፡ በዋጋ-ቢስ እውነትና በሐሰት መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ ርቀቱ የጋት ያህል ነው ይላሉ እውቁ የንግድ ሰው ወልደሔር ይዘንጋው በግለ ታሪክ መጽሐፋቸው፡፡

ገረዲቱ - ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት

Image
ገረዲቱ እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ በጎም ሆነ ደግ ታሪክ ሳይስተናገድበት አያልፍም፤ በሥነ ፍጥረት ታሪክ ውስጥ ብትመለከቱ ምንም ሳይሠራ ያለፈ ሰው ታገኙ ይሆናል እንጅ ምንም ሥራ ያልተሠራበት ቀን አታገኙም፤ ምክንያቱም ጊዜ የተፈጠረው ለሥራ ነውና:: ከመጀመሪያዋ ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር ያላ ሥራ ያሳለፋት ጊዜ አትገኝም፡፡ በእያንዳንዳችንም ሕወት ውስጥ እለታት የየራሳቸው የሆነ ልዩ ልዩ ታሪክ አላቸው፡፡ አንዳንዶቹ የወደቅንባቸው አንዳንዶቹ የተነሣንባቸው፣ የተደሰትንባቸውና ያለቀስንባቸው፣ እግዚአብሔርን  ያገኘንባቸው ወይም ከሰይጣን ጋር ማኅበርተኛ የሆንባቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡  ለዛሬው እንኳን ይህን የምላችሁ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፊ ታሪክ ስለተመዘገበለት አንድ ቅዱስ ሰው ልነግራችሁ ፈልጌ ነው፤ ሰውየው ገሊላዊ፣ ትውልዱና ነገዱ ዕብራዊ ሲሆን ያደገው በታላቁ የገሊላ ባሕር አጠገብ ነው ዋና ሥራው አሣ አጥማጅነት ሲሆን የቀደመ ስሙ ስምዖን ወልደ ዮና የክርስትና ስሙ ደግሞ ጴጥሮስ ይባላል፡፡ ይህ ሰው እግዚአብሔር በእርጅና ዘመኑ የባረከው ሰው ነው፤ መቸም እግዚአብሔር ለእያንዳንደችን ያዘጋጃት የመጎብኘት ቀን እንዳለች እናምናለን፣ ከዚህም የተነሣ አንዳንዶችን  በማሕጸን ሳሉ እንደነ ኤርምያስና ዮሐንስ መጥምቅ ያሉትን፣አንዳንዶችን በጨቅላነት እድሜ እንደነ ቅዱስ ቂርቆስ፣ አንዳንዶችን በወጣትነት እንደነ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊና እንደነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያሉትን አንዳንዶችን በእርጅና ዘመናቸው እንደነ ቅዱስ ጴጥሮስ ያሉትን ጎብኝቷቸዋል ፡፡ ከሰው የሚጠበቅ የሚጎበኝበትን ቀን ደጅ መጥናት ነው እንጅ ሌላው የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እግዚአብሔር የወሰነለት ቀን ስትደርስ በትጋት ሆኖ ከሚሠራበት ቦታ ሂዶ ጎበኘው፣ ለ...

አትነካኪኝማ

Image
  ተይ አትነካኪኝ አትቀስቅሽኝ እቴዋ ትዝታችን ላይ ነው የተኛሁ የጊዜን ምንጣፍ አንጥፌ አትነካኪኝ ልረፍበት አትቀስቅሽኝ ከእንቅልፌ አትወስዉሽኝ እቴዋ ከነካካሽኝማ በጊወርጊስ በተስኪያን በመንገዱ ዳር አልፌ አደባባዩን ዙሬ በዘንባባው ጥግ ታጥፌ አንድ ጊዜ ካፌው በር ላይ ሌላ ጊዜ መናፍሻው እዚያ ከወፎች መንደር እዚያ ከፍቅር ዋሻው መናፈሻው… አስታውስሺው? ሌላ ጊዜ ከሰፈርሽ ሌላ ጊዜ ከሰፈሬ ከተሰገሰገበት ሚስጥርሽና ሚስጥሬ ሌላ ጊዜ በጸሃዩ ሌላ ጊዜ በምሽቱ መጨለሙን መች አስቤው ልቤ ያለ ከመንጋቱ፡፡ ታስታዉሻልሽ ግን… ከጠዋቷ ጸሃይ ጋር እኩል ነበር ምጠብቅሽ ልቤን ቅልጥ የምትለው አንድም በብርሃኗ አንድም  ደግሞ በፈገግታሽ፡፡ አትነካኪኝ እቴዋ ከነካካሽኝማ ትናንትናን እያሰብኩ ነገየን እየረገጥኩ ህልሜን እየደፈጠጥኩ ተስፋየን እየገደልኩ በሃሳብ ሽምጥ ግልቢያ ትናንት ላይ እደርሳለሁ ያንን ጊዜ አነሳለሁ ድሮአችንን አነግሳለሁ አሁኔን እቀብረዋለሁ በዛሬ ጀምበር ላይ ቆሜ ትዝታሽን እኖራለሁ፡፡ አትወስዉሽኝ አለሜ ዛሬ ላይ ተገትሬ ልጅነታችንን ያሰብኩለት ያ መነፋፈቃችን ያ መፈላለጋችን የመዋደዳችን ግለት በጊዜ ምድጃ ላይ ቀናትን እያነደደ ትዝታ የሚባል ጉቶ እቶኑ ዉስጥ እየማገደ የፍቅርን ፍም እሳት ያፈልቃል ደክሞት የተኛን ገላ፣ የተኛን ልብ ያሞቃል፡፡ አታስታዉሽኝ እቴዋ አታሰሚኝ ድምጽሽን አታሳይኝ ከንፈርሽን አታስታዉሽኝ ፈገግታሽን …ጥርስሽን ያሰብኩለት ተደርድረው በመደዳ ከህሌናየ ላወጣሽ ለራሴ የማልኩትን ቃልን ነው የምከዳ!!! ተይ አትነካኪኝማ ተይ አትወስዉሺኝማ ተይ አትቀስቅሺኝማ ተይ ተይ ተይ                ...

ከላሊበላ ሰማይ ስር Lalibela

Image
አሁን ይህንን ስጽፍልህ 100 ግራም ገለምሶ ይዤ ከተቀመጥኩበት ቦታ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ አንተም ከዚህ የተለየ ነገር እያደረግህ እንዳልሆነ ስነግርህ ያለጥርጥር ነው፡፡ ግድ የለም በርጫ ሙድ ላይ አይደለህም እንበል…ግን የሰፈር አረቄ ቤት ዉስጥ አረቄን በሲጋራና   በአሉባልታ እያወራረድክ ነው፡፡ እሱ ላይ ባትሆንም ደግሞ መንገድ ላይ ድድ እያሰጣህ   አላፊ አግዳሚ ታሸማቅቃለህ…ትለክፋለህ፣ትስቃለህ……መሳቂያ!!! በሌለንበት በሃሜት…   ላልከኝ ወዳጄ ደግሜ እልሃለሁ አትፍራ ከማማት ልቆጠብና ቢሮ ዉስጥ ነህ እንበል ግን ቢሮህ ዉስጥ ብትሆንም ወንበር እያለፋህ የምሳ ሰዓት መድረስን ትጠባበቅ ይሆናል ወይም ደግሞ ልክ እንደ ጀበና ቡና ኮምፒተር ላይ ተጥደሃል   ማለቴ ፌስ ቡክ ላይ፡፡ እና እልሃለሁ ቢሮ ዉስጥ ሆነህ ስራ ካልሰራህ ጫት ቤት ከተቀመጠው … መንገድ ላይ ድድ ከሚያሰጣው በምን ልለይህ…አረቆ ከሚጋተውስ በምን ተሸልክ….በምንም!! ብቻ የትም ሁን የት ብትሰራም ባትሰራም ቅሉ የዚህ ትዉልድ አባል ነህ፡፡ ይቅርታ የስድብ ናዳ አወረድኩኝ ልበል ምን ላድርግ በቆምኩበት ብትቆሙ ያየሁትን ብታዩኮ እንደ እሳት ላንቃ የሚገርፍ የማንነት ስሜት ከዉስጣችሁ ሲገነፍል ታዩት ነበር፡፡ ወዳጄ አሁን በላሊበላ ተራሮች ስር ነኝ፡፡የንጉስ ላሊበላ የእጅ ስራና ጥበብ ካረፈባቸው ድንቅ ዉቅሮች ስር፡፡ ግን ምን ያደርጋል ማመን አቃተኝ፡፡ -የሰው ልጅ እንዴት ከአንድ ድንጋ እነዚን ግዙፍ አቢያተክርስቲያናት ሊሰራ ይችላል….እኛምኮ የሰው ዘሮች ነን አዷማ ይዘን፣በዲጅኖ ታግዘን በመዶሻ ደብድነብ ሜ አንድ ሜትር ድንጋይ ፈለጥንና -እነዚ በድንጋይ ላይ የተጠረቡ ቅርጻቅርጾችና አምሳላት እንዴት እዉን ሊሆኑ ቻሉ -እነዚያ 900 በላይ አመታትን ...

ሳስበው ደከመኝ

Image
ሴትን ልጅ ስትመርጣት አጋር ለህይወትህ ዉስጥ ዉበቷን እንጂ ዉጯ እንዳያስትህ እኔም እንዲሁ ነኝ ዉበት ረጋፊ ነው  ዉስጤን ተመልከተኝ ብለሽኝ ነበረ… ግና….. ከባለጌ ጡትሽ መረን ከለቀቀው ከቀዩ ከንፈርሽ ከተለቀለቀው ከሸምበቆ ባትሽ እንደ ፍም ከቀላው ከፌዘኛ ሳቅሽ አዉሬ ከሚያስበላው ከአሽሙረኛ ዳሌሽ በኩራት ከሰፋው ከሱናሜ ጥቅሻሽ መንገድ ከሚያስጠፋው ፤፤ ፤፤ ዙሪያ ገባሽ ሁሉ ከልሎት የአጋም ሾህ አጥረሽው በአጣና በየት አልፌ ነው ጸባይሽን የማየው  ውስጥሽን ማጠና!? እ….. ሳስበው ደከመኝ!!! Hab. A

የህልሜ ጓደኛ 3

Image
ከክፍል 2 የቀጠለ....  Part 1 link , part 2 link ‹‹ስለአንተ ሁሉን ነገር ነግሬዋለሁ፡፡ ከተዋወቅን ስድስት ወር እንደሆነን… ስንቀሳቀስ ሁሌም የአንተን ባጃጅ እንደምጠቀም… የምፈልገው ቦታ እንደምታደርሰኝና እንደምትመልሰኝ… ከለካፊዎች እንደምትጠብቀኝ… እንደምታዝናናኝ… እንደምታጫዉተኝ… ባጃጅ መንዳት እንደምታለማምደኝ… እና ደግሞ…›› የጀመረችውን ዓረፍተ ነገር ሳትጨርሰው አይኗን እንደጨፈነች ተመስጣ ጥርሷን ብቻ ስታሳየኝ ቆየች፡፡ ከዚያ አይኞቿ ተከፈቱ፡፡ ‹‹…እና ደግሞ… እንደ.ም.ወ.ድ.ህ ጭምር!›› በጠራራ ፀሀይ… ወለል ባለ ብርሀን… የሚርመሰመስ ህዝብና መኪና ባለበት መንገድ ዳር… በዚህ ሁሉ መሀል እኔነቴን ማን ዘረፈኝ? ድምፄንስ ምን ዘጋው? ምክንያቱን ሳላውቀው ድጋሚ ጸጥ አልኩ፡፡ ድርቅ እንደ እንጨት! ከኋላየ መጥታ እጇን ጫን ስታደርግብኝ ባለሁበት ቅዠቴ ጀመረኝ፡፡ የተቀደሰ ቅዠት፡፡ ቅዠቱ እንዲህ ሲል ይጀምራል፡- እኔና ሳሮን ነጭ በነጭ ሙሉ የባህል ልብስ ለብሰን፣ መላዕክቱን መስለን በተቆናጀች ባጃጄ ወደ አባቷ ቤት እንቀርባለን፡፡ አባቷ ነጭ በነጭ የሆነ ሙሉ የባህል ልብስ ለብሰው የቤታቸው ሰገነት ላይ በሩቁ ይታዩናል፡፡ የሆኑ ከየት መጡ ያላልናቸው ሁለት ነጭ መለዮ የለበሱ ሰዎች ሳሮንና እኔን ግራና ቀኝ አጅበው ወደ አባቷ አቀረቡን፡፡ /ያ-ቅዠት የት ሄደ? ያ- የሰይጣኖቹ?/ ሳሮን እሮጣ ሄዳ አባቷን ጥምጥም ብላ ከሳመቻቸው በኋላ ወደኔ እየጠቆመች ‹‹አባየ የነገርኩህ ልጅ ይኼ ነው›› ስትላቸው ከሳሮን በፈጠነ ሮጬ እግራቸው ስር ተደፍቼ ጉልበት ሳምኩ፡፡ ከየት መጣ ያላልኩት ወታደር ከእግራቸው ስር ለአክብሮት የተንበረከክሁትን እኔን በአንድ እጁ አንጠልጥሎ አነሳኝ፡፡ እንደ ሁኔታው እንዳንጠለጠለኝ ሊወረውረኝ ያሰበ ይመስል ነ...

የህልሜ ጓደኛ 2

Image
 (ከክፍል 1 የቀጠለ...) Part 1 link የሳምንቱን ቀናት በሙሉ በስራ ነው የማሳልፈው፡፡ ሰው ሳደርስ ሰው ስመልስ፡፡ ቢሆንም ግን የሰንበት ቀናት አልፈው ሰኞ ሲመጣ እኔም ልክ ሁለት ቀን እረፍት እንደቆየ ሰራተኛ ሁሉ በሞራል እና በወኔ አዲስ ሰው ሁኜ ለስራ እነሳለሁ፡፡ የመንግስት ሰራተኛው ቅዳሜና እሁድን እረፍት አድርጎ ሰኞን በአዲስ መንፈስ ሲቀላቀል እኔ ምንም እረፍት ሳይኖረኝ ሁሌም ልክ እንደ ሰራተኞች በአዲስ መንፈስ ነው የምቀበለው፡፡ ዛሬ ግን ሰኞ አስቀየመኝ፡፡ እንደ ድሮው በአዲስ መንፈስ ልቀበለው ተዘጋጅቼ ወደ ባጃጅ ሽቀላየ ስወጣ እሱ ግን ፊቱን አጨፈገገብኝ፡፡ የስራ መንፈሴን አቆሸሸው፡፡ ፈረንጆች ሰኞን ‹‹ብላክ መንደይ/ጥቁሩ ሰኞ/›› ይሉታል ሲባል ከሰኞ ጋር የቆየ ቂም ይኖራቸው ይሆናል እላለሁ፡፡ ምናልባት ፋሽስት ጣሊያን በሃብሻ አርበኞች ድባቅ የተመታበት ሰኞ ቀን ቢሆንስ? ለዚያ ይሆናል ሰኞን የሚጠሉት፡፡ እኔ ግን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ሰኞን ከማክሰኞና ከቅዳሜ ለይቸ አላየውም- ያው እንደ ሌሎች ቀናት ሰኞም ቀን ነው፡፡ ሰኞም ባጃጅ ላይ እሰራለሁ፤ ማክሰኞም፣ ረቡዕም፣ አርብም… ወ.ዘ.ተ እንደተለመደው፡፡ ዛሬ ብቻ ነው ሰኞ ጥቁር የሆነብኝ ‹ብላክ መንደይ›! ጠዋት እንደተለመደው እንጀራ ፍርፍር ሰርቼ ቁርስ አድርጌ ልወጣ ሽንኩርት ከትፌ፣ ዘይት ጨምሬ ልክ በርበሬ ልጨምር ስል መብራት ድርግም አለ፡፡ ምን አለበት በርበሬ እስክጨምር ድረስ እንኳን ቢታገሰኝ? ይኸው የዛሬን ሰኞ ሳልፈልግ ለመፆም አቋም ያዝኩ፡፡ በቀጥታ ወደ ባጃጅ ስራየ በመግባት በመስመር ወረፋ ጠብቄ አራት ያህል ቢያጆ ከመስራቴ ባጃጄ መንገድ ላይ ተንተፋትፋ ቆመች፡፡ እንደ ዛሬ አማርሬ አላውቅም፡፡ በቃ ሰኞን ጠላሁት… black Monday ብቻ ሳይሆን የሆነ ‹...