Posts

ከላሊበላ ሰማይ ስር Lalibela

Image
አሁን ይህንን ስጽፍልህ 100 ግራም ገለምሶ ይዤ ከተቀመጥኩበት ቦታ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ አንተም ከዚህ የተለየ ነገር እያደረግህ እንዳልሆነ ስነግርህ ያለጥርጥር ነው፡፡ ግድ የለም በርጫ ሙድ ላይ አይደለህም እንበል…ግን የሰፈር አረቄ ቤት ዉስጥ አረቄን በሲጋራና   በአሉባልታ እያወራረድክ ነው፡፡ እሱ ላይ ባትሆንም ደግሞ መንገድ ላይ ድድ እያሰጣህ   አላፊ አግዳሚ ታሸማቅቃለህ…ትለክፋለህ፣ትስቃለህ……መሳቂያ!!! በሌለንበት በሃሜት…   ላልከኝ ወዳጄ ደግሜ እልሃለሁ አትፍራ ከማማት ልቆጠብና ቢሮ ዉስጥ ነህ እንበል ግን ቢሮህ ዉስጥ ብትሆንም ወንበር እያለፋህ የምሳ ሰዓት መድረስን ትጠባበቅ ይሆናል ወይም ደግሞ ልክ እንደ ጀበና ቡና ኮምፒተር ላይ ተጥደሃል   ማለቴ ፌስ ቡክ ላይ፡፡ እና እልሃለሁ ቢሮ ዉስጥ ሆነህ ስራ ካልሰራህ ጫት ቤት ከተቀመጠው … መንገድ ላይ ድድ ከሚያሰጣው በምን ልለይህ…አረቆ ከሚጋተውስ በምን ተሸልክ….በምንም!! ብቻ የትም ሁን የት ብትሰራም ባትሰራም ቅሉ የዚህ ትዉልድ አባል ነህ፡፡ ይቅርታ የስድብ ናዳ አወረድኩኝ ልበል ምን ላድርግ በቆምኩበት ብትቆሙ ያየሁትን ብታዩኮ እንደ እሳት ላንቃ የሚገርፍ የማንነት ስሜት ከዉስጣችሁ ሲገነፍል ታዩት ነበር፡፡ ወዳጄ አሁን በላሊበላ ተራሮች ስር ነኝ፡፡የንጉስ ላሊበላ የእጅ ስራና ጥበብ ካረፈባቸው ድንቅ ዉቅሮች ስር፡፡ ግን ምን ያደርጋል ማመን አቃተኝ፡፡ -የሰው ልጅ እንዴት ከአንድ ድንጋ እነዚን ግዙፍ አቢያተክርስቲያናት ሊሰራ ይችላል….እኛምኮ የሰው ዘሮች ነን አዷማ ይዘን፣በዲጅኖ ታግዘን በመዶሻ ደብድነብ ሜ አንድ ሜትር ድንጋይ ፈለጥንና -እነዚ በድንጋይ ላይ የተጠረቡ ቅርጻቅርጾችና አምሳላት እንዴት እዉን ሊሆኑ ቻሉ -እነዚያ 900 በላይ አመታትን ...

ሳስበው ደከመኝ

Image
ሴትን ልጅ ስትመርጣት አጋር ለህይወትህ ዉስጥ ዉበቷን እንጂ ዉጯ እንዳያስትህ እኔም እንዲሁ ነኝ ዉበት ረጋፊ ነው  ዉስጤን ተመልከተኝ ብለሽኝ ነበረ… ግና….. ከባለጌ ጡትሽ መረን ከለቀቀው ከቀዩ ከንፈርሽ ከተለቀለቀው ከሸምበቆ ባትሽ እንደ ፍም ከቀላው ከፌዘኛ ሳቅሽ አዉሬ ከሚያስበላው ከአሽሙረኛ ዳሌሽ በኩራት ከሰፋው ከሱናሜ ጥቅሻሽ መንገድ ከሚያስጠፋው ፤፤ ፤፤ ዙሪያ ገባሽ ሁሉ ከልሎት የአጋም ሾህ አጥረሽው በአጣና በየት አልፌ ነው ጸባይሽን የማየው  ውስጥሽን ማጠና!? እ….. ሳስበው ደከመኝ!!! Hab. A

የህልሜ ጓደኛ 3

Image
ከክፍል 2 የቀጠለ....  Part 1 link , part 2 link ‹‹ስለአንተ ሁሉን ነገር ነግሬዋለሁ፡፡ ከተዋወቅን ስድስት ወር እንደሆነን… ስንቀሳቀስ ሁሌም የአንተን ባጃጅ እንደምጠቀም… የምፈልገው ቦታ እንደምታደርሰኝና እንደምትመልሰኝ… ከለካፊዎች እንደምትጠብቀኝ… እንደምታዝናናኝ… እንደምታጫዉተኝ… ባጃጅ መንዳት እንደምታለማምደኝ… እና ደግሞ…›› የጀመረችውን ዓረፍተ ነገር ሳትጨርሰው አይኗን እንደጨፈነች ተመስጣ ጥርሷን ብቻ ስታሳየኝ ቆየች፡፡ ከዚያ አይኞቿ ተከፈቱ፡፡ ‹‹…እና ደግሞ… እንደ.ም.ወ.ድ.ህ ጭምር!›› በጠራራ ፀሀይ… ወለል ባለ ብርሀን… የሚርመሰመስ ህዝብና መኪና ባለበት መንገድ ዳር… በዚህ ሁሉ መሀል እኔነቴን ማን ዘረፈኝ? ድምፄንስ ምን ዘጋው? ምክንያቱን ሳላውቀው ድጋሚ ጸጥ አልኩ፡፡ ድርቅ እንደ እንጨት! ከኋላየ መጥታ እጇን ጫን ስታደርግብኝ ባለሁበት ቅዠቴ ጀመረኝ፡፡ የተቀደሰ ቅዠት፡፡ ቅዠቱ እንዲህ ሲል ይጀምራል፡- እኔና ሳሮን ነጭ በነጭ ሙሉ የባህል ልብስ ለብሰን፣ መላዕክቱን መስለን በተቆናጀች ባጃጄ ወደ አባቷ ቤት እንቀርባለን፡፡ አባቷ ነጭ በነጭ የሆነ ሙሉ የባህል ልብስ ለብሰው የቤታቸው ሰገነት ላይ በሩቁ ይታዩናል፡፡ የሆኑ ከየት መጡ ያላልናቸው ሁለት ነጭ መለዮ የለበሱ ሰዎች ሳሮንና እኔን ግራና ቀኝ አጅበው ወደ አባቷ አቀረቡን፡፡ /ያ-ቅዠት የት ሄደ? ያ- የሰይጣኖቹ?/ ሳሮን እሮጣ ሄዳ አባቷን ጥምጥም ብላ ከሳመቻቸው በኋላ ወደኔ እየጠቆመች ‹‹አባየ የነገርኩህ ልጅ ይኼ ነው›› ስትላቸው ከሳሮን በፈጠነ ሮጬ እግራቸው ስር ተደፍቼ ጉልበት ሳምኩ፡፡ ከየት መጣ ያላልኩት ወታደር ከእግራቸው ስር ለአክብሮት የተንበረከክሁትን እኔን በአንድ እጁ አንጠልጥሎ አነሳኝ፡፡ እንደ ሁኔታው እንዳንጠለጠለኝ ሊወረውረኝ ያሰበ ይመስል ነ...

የህልሜ ጓደኛ 2

Image
 (ከክፍል 1 የቀጠለ...) Part 1 link የሳምንቱን ቀናት በሙሉ በስራ ነው የማሳልፈው፡፡ ሰው ሳደርስ ሰው ስመልስ፡፡ ቢሆንም ግን የሰንበት ቀናት አልፈው ሰኞ ሲመጣ እኔም ልክ ሁለት ቀን እረፍት እንደቆየ ሰራተኛ ሁሉ በሞራል እና በወኔ አዲስ ሰው ሁኜ ለስራ እነሳለሁ፡፡ የመንግስት ሰራተኛው ቅዳሜና እሁድን እረፍት አድርጎ ሰኞን በአዲስ መንፈስ ሲቀላቀል እኔ ምንም እረፍት ሳይኖረኝ ሁሌም ልክ እንደ ሰራተኞች በአዲስ መንፈስ ነው የምቀበለው፡፡ ዛሬ ግን ሰኞ አስቀየመኝ፡፡ እንደ ድሮው በአዲስ መንፈስ ልቀበለው ተዘጋጅቼ ወደ ባጃጅ ሽቀላየ ስወጣ እሱ ግን ፊቱን አጨፈገገብኝ፡፡ የስራ መንፈሴን አቆሸሸው፡፡ ፈረንጆች ሰኞን ‹‹ብላክ መንደይ/ጥቁሩ ሰኞ/›› ይሉታል ሲባል ከሰኞ ጋር የቆየ ቂም ይኖራቸው ይሆናል እላለሁ፡፡ ምናልባት ፋሽስት ጣሊያን በሃብሻ አርበኞች ድባቅ የተመታበት ሰኞ ቀን ቢሆንስ? ለዚያ ይሆናል ሰኞን የሚጠሉት፡፡ እኔ ግን እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ሰኞን ከማክሰኞና ከቅዳሜ ለይቸ አላየውም- ያው እንደ ሌሎች ቀናት ሰኞም ቀን ነው፡፡ ሰኞም ባጃጅ ላይ እሰራለሁ፤ ማክሰኞም፣ ረቡዕም፣ አርብም… ወ.ዘ.ተ እንደተለመደው፡፡ ዛሬ ብቻ ነው ሰኞ ጥቁር የሆነብኝ ‹ብላክ መንደይ›! ጠዋት እንደተለመደው እንጀራ ፍርፍር ሰርቼ ቁርስ አድርጌ ልወጣ ሽንኩርት ከትፌ፣ ዘይት ጨምሬ ልክ በርበሬ ልጨምር ስል መብራት ድርግም አለ፡፡ ምን አለበት በርበሬ እስክጨምር ድረስ እንኳን ቢታገሰኝ? ይኸው የዛሬን ሰኞ ሳልፈልግ ለመፆም አቋም ያዝኩ፡፡ በቀጥታ ወደ ባጃጅ ስራየ በመግባት በመስመር ወረፋ ጠብቄ አራት ያህል ቢያጆ ከመስራቴ ባጃጄ መንገድ ላይ ተንተፋትፋ ቆመች፡፡ እንደ ዛሬ አማርሬ አላውቅም፡፡ በቃ ሰኞን ጠላሁት… black Monday ብቻ ሳይሆን የሆነ ‹...

የህልሜ ጓደኛ 1

Image
ቤታቸው ከአራት ኪሎ ቤተ-መንግስት የሚተናነሰው ጠቅላይ ሚንስተሩ እዚያው ባለመኖራቸው ብቻ ነው፡፡ ልጥጥ ያለች የባለሀብት ልጅ፡፡ ያውም የባለስልጣን፡፡ ግቢያችውን ላስተዋለው አንድን የተከበረ ጫካ በማን አለብኝነት ወርሰውና መሀሉን አስመንጥረው መኖሪያቸውን እዚያ የመሰረቱ ይመስላል፡፡ ከውጭ ሆኖ ለተመለከተው ግቢው የቤተ-ክርስቲያን ቅጽር ወይም የሆነ ፓርክ ይመስላል፡፡ ግቢውን ከከተማው አስፓልት የሚያገናኝ አንድ ጠበብ ያለ የአስፋልት መንገድ አለ፡፡ መንገዱ ከዋናው መስመር ይገነጠልና ከሁለት እሰከ ሶስት የሚሆኑ የሚያማምሩ ቤቶችን ካለፉ በኋላ ቀጥ ባለ አስፋልት ወደነ ሳሮን ቤት ያደርሳል፡፡ አሰፋልቱ ግራና ቀኝ በተተከሉና ቅጠላቸውን በታቀፉ ዛፎች መካካል የተዘጋ ነው፡፡ ማዶና ማዶ ያሉት ዛፎች ወዳጅነት መስርተው በአየር ላይ ቅርንጫፎቻቸውን አስተቃቅፈዋል፡፡ ውስጥ ለውስጥ በአስፋለት መንገዱ አብዛኛውን ጊዜ ሁለት መኪኖች ሽር እያሉ ይወጣሉ ወይም ይገባሉ፡፡ አንደኛው የአባቷ ፕራዶ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በብዛት እሷ የምትነዳው ራቫ ፎር፡፡ ከግቢው አጠገብ ዘበኛው አይጠፋም፡፡ ዘበኛው ማለት የሚከብድ ቢሆንም ያው ዘበኛ ስለሆነ ምንም ሊባል አይችልም፡፡ የሚያምር ጥቁር ጨርቅ ሱሪ ከነጭ ሸሚዝ ጋር ለብሷል፡፡ ካራቫት አላሰረም፤ የላይኞቹ ሁለት የሸሚዙ ቁልፎች አልተቆለፉም፡፡ የሸሚዙ ያለመቆለፍ ከአንገቱ ላይ ላንጠለጠለው የብር ሀብል የተመቸው ይመስል ሀብሉ ደረቱ ላይ ያብረቀርቃል፡፡ ዘበኛነቱን ያወቅሁት እንግዳ ሲመጣ በር ሲከፍትና መኪና ከወጣ በኃላ መልሶ በር ሲቆልፍ ነው፡፡ ልዩ የሆነ ስነ-ምግባር አለው፡፡ የሸሚዙን እጅጌ በሁለት ጊዜ ድግግሞሽ ወደ ላይ ቀንፎታል፡፡ ክንዱ አካባቢ ያለው የእጁ ዉፍረትና የሰፋው ደረቱ ላይ ማራኪ ባህሪው ታክሎበት በወታደራዊ ስነምግባ...

የከሸፈ ትውልድ 3

Image
የመጨረሻው ክፍል Last Part ከዚህ ርዕስ ሳልወጣ አንድ ወርክሾፕ ላይ የታዘብኩትን ገጠመኝ ላካፍልህ፡፡ አወያዩ የሆነ ጠንከር ያለ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሲያወያዩን ከቆዩ በኋላ ‹…እስኪ ቤታችሁ ዉስጥ የእናት ሀገራችሁን ሰንደቅ አላማ የሰቀላችሁ ወይም ያስቀመጣችሁ?› ብሎ ጠየቀ፡፡ ከአዳራሽ ሙሉ ተሰብሳቢ መካከል አንድ እንኳን ‹እኔ› ብሎ እጁን ያወጣ አልነበረም፡: (የክፍል 1 ሊንክ) (የክፍል 2 ሊንክ ) ሰዉየው በአግራሞት እየተመለከተን ‹ባንዲራ ቤቱ ያለው የለም?› ሲል ድጋሜ ጠየቀ፡፡ አሁንም ጸጥታ እንጂ ምላሽ አልነበረም፡፡ ሰዉየው ፈገግ ብሎ ንግግሩን ቀጠለ ‹እሽ! የድሮው ባንዲራም ቢሆን?› ሲል ሶስት እድሜ ጠገብ አባቶችና ብዛት ያላቸው ወጣቶች እጃቸውን አወጡ፡፡ ከአጠገቤ የተቀመጠ አንድ ወዳጄ ‹አየህ በሰንደቅአላማችን እንኳን አልተስማማንበትም፤ ይገርማል! የዚች እንቆቅልሽ የሆነች አገር ጉዳይ!› ያለኝን አልረሳዉም፡፡ የሆሊዉድና ቦዉሊድ ፊልም ሰሪዎች ፊልማቸው ዉስጥ አንድም ቀን ስለ እርሻ ስራቸው፣ ስለ አዘራራቸውና ስለ ምርት አሰባሰባቸው አሳይተዉን አያዉቁም፡፡ በተቃራኒው ግን የቡድን ወሲባቸውን፣ ባዕድ አምልኮታቸውንና መረን የለቀቀ ተግባራቸውን ያስኮመኩሙናል፡፡ ዝሙትን፣ ሱስን፣ ስርቆትንና መገዳደልን ይግቱናል፡፡ ተንኮላቸውን እያሰረጹብን እንደሆነ ግን የሚረዳ ትዉልድ የለም፡፡ ግዕዝ ቋንቋችን በጠራራ ፀሃይ ሲዘረፍ ‹‹የዘራፊ ያለሽ ኡ ኡ›› ብሎ ድምጹን ያሰማ አካል የለም፡፡ ከእኛው ምድር በቅሎ ለዘመናት የተመገብነውን ጤፋችንን አይናችን እያየ ‹‹ባለቤት አይደላችሁም፤ ባለቤቶቹ ኔዘርላንዶች ናቸው!›› ስንባል ‹‹ትክክል ናችሁ›› በሚል አይነት እግራችንን አጣጥፈን ተቀምጠናል፡፡ ምን አዚም እንደተደረገብን አላዉቅም፡፡ እነሱኮ የበይ ተመልካቾች አድር...

የከሸፈ ትውልድ 2

Image
ክፍል 2 - Part 2 ከወራት በኋላ የቀን ዉሎ ማስታዎሻየ ላይ የተጻፉ ነገሮችን እያገላበጥኩ ስመለከት የፕሮፌሰሩን ንግግሮች አገኘኋቸው፡፡ ጊዜ መስጠት አልፈለግሁም፤ ወዲያው ስልኬን አዉጥቼ ለፕሮፌሰር ደወልኩላቸው:: (ክፍል 1 ን ለማንበብ ይጫኑ) ከፕሮፌሰር ሙሴ ጋር ከዩኒቨርሲቲው ግቢ ዉስጥ ከሚገኘው የመምህራን መዝናኛ ክበብ ቡና እየጠጣን ብዙ ነገሮችን ተጨዋወትን፡፡ ለዛሬው ብዙ አድማጭ እንጂ ብዙ ተናጋሪ አልነበርኩም፡፡ የዩኒቨርስቲው ግቢ ደስ ይላል፡፡ ከመንገዱ ዳርና ዳር የሚገኙት ዛፎች ቅርንጫፍ ለቅርንጫፍ ተቃቅፈዋል፡፡ በዚያ ላይ ቅዝቃዜው፡፡ ቀጭኑን የአስፋልት መንገድ የግራ ጠርዝ ይዘን ከፕሮፌሰር ጋር ወደ ግቢው መሃል ዘለቅን፡፡ ግቢው አድሮ አዲስ ነው፡፡ ሲያምርና ሲፈካ ነው የሚያድረው፡፡ የተማርኩበት ግቢ … በተለምዶ ጆኮ ስኩል /Joco school/ ተብሎ የሚጠራው ህንጻ … አለፍ ሲል የተፈጥሮ ሳይንስ ቤተ መጽሃፍት … እነዚህ ብቻ ናቸው ባሉበት ያገኘኃቸው፡፡ ያኔ ተማሪዎች እያለን እንደነበረው ከነ ሙሉ ዉበታቸው አሉ፡፡ አዲስ ነገር የተጨመረው ከቤተ መጽሃፍቱ ጎንና ዙሪያውን የተሰሩት የብረት ጠረንጴዛና ወንበሮች ናቸው፡፡ ‹‹… ተመልከት ይሄ ሰነፍ ተማሪዎች እንደ አሸን የሚፈሉበት ዋሻ ነው ›› አሉኝ ፕሮፌሰር፤ ተማሪዎቹ አንድ ለአምስት እየተደራጁ ወደሚወያዩበት ክብ ሰርተው የተደረደሩ ወንበሮች እንድመለከት እየጋበዙኝ፡፡ ቤተ መጽሃፍቱ አካባቢ በሚገኙት አረንጓዴ ዛፎች መካከል ባሉት ክፍት ቦታዎች አለፍ ...